ተረት ፈ

ከWikipedia

  • ፈላ ገነፈለ ተሞላ ጎደለ
  • ፈረሰኛ ሲሮጥ እግረኛን ምን አቆመው
  • ፈረሰኛ ሲሸሽ እግረኛን ምን አመጣው
  • ፈረሰኛ የወሰደውን እግረኛ አይመልሰውም
  • ፈረሱም ይኸው ሜዳውም ይኸው
  • ፈረስ ሲያጠብቅ ልጓም አይለቀቅ
  • ፈረስ በራሪ በቅሎ ሰጋሪ
  • ፈረስ ቢያነክስ አህያ ታጉዝ
  • ፈረስ ቢጠፋው ኮርቻውን ገልቦ አየ
  • ፈረስ አውቃለሁ ስገታ እወድቃለሁ
  • ፈረስና ገብስ ያጣላል
  • ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም
  • ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል በቅሎ ጥሎ ይረግጣል
  • ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል አህያ ጥሎ ይረግጣል
  • ፈረንጆች እንደመርፌ ይገቡ እንደዋርካ ይሰፉ
  • ፈሩ ፈሩ ማጀት አሩ
  • ፈሩ ፈሩ ማጀት አደሩ
  • ፈሪ ለናቱ
  • ፈሪ ለናቱ ይገባል
  • ፈሪ ለናቱ ጀግና ለጀግንነቱ
  • ፈሪ በገዛ ጠቡ ገላጋይ ይሆናል
  • ፈሪ ቢሸፍት እስከ ጓሮ
  • ፈሪ እንዳይሉኝ አንድ ገደልሁ ጀግናም እንዳይሉኝ አልደገምሁ
  • ፈሪ ከውሀ ውስጥ ያልበዋል
  • ፈሪ ካልጋ ላይ ይወድቃል
  • ፈሪ ካልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል
  • ፈሪን ውሀ ውስጥ ያልበዋል
  • ፈሪ ውሀ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል
  • ፈሪ ውሀ ውስጥ ያልበዋል
  • ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል
  • ፈሪ የናቱ ልጅ ነው
  • ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
  • ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢተኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
  • ፈርተው ድንጋይ ሲጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
  • ፈርተው ድንጋይ ቢጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
  • ፈርተው ድንጋይ ቢወረውሩ ጅብ ወጣ ከዱሩ
  • ፈሷን ፈስታ ቂጧን ጨበጠች
  • ፈስ በወረንጦ እየተለቀመ ነው
  • ፈስቶ ቂጥን መያዝ
  • ፈስ ያለበት ቂጥ ዝላይ አይችልም
  • ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም
  • ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስራል
  • ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስቀራል
  • ፈክሮ መሽሽ ታሪክ ያበላሻል
  • ፈዛዛ እያንቀላፋ ይገባል ፈፋ
  • ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስቲበርድ ይራበኝ
  • ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስኪበርድ ይራበኝ
  • ፈገግታ የልብ አለኝታ
  • ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ርስትን ያህል ቦታ
  • ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ
  • ፈጥነው የገመዱት ፈጥኖ ይበጠሳል
  • ፈጥኖ መስጠት ኋላ ለመጸጸት
  • ፈጥኖ መስጠት ቶሎ ለመጸጸት
  • ፈጥኖ መስጠት በኋላ መጸጸት
  • ፈጭታ የነበረች ላመልማሎ ኮራች
  • ፊት ያሞጠሙጧል ኋላ ያፏጩዋል
  • ፍሪክና ጻድቅ አይቀጣጠርም
  • ፍሬ በመስጠቱ ባልታወቀ ሾላ የወፎች ዝማሬ ቀደመ አሉ
  • ፍቅር ሲጠና ቆሎ ያጓርሳል
  • ፍቅርና ጉርሻ ካላስጨነቀ አያምርም
  • ፍቅር ካለ ዘጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል
  • ፍቅር ፍቅር ሲሉ ደሀ ሆነው ቀሩ
  • ፍየል ሁለት ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
  • ፍየል ላምስት ዶሮ ለባልና ለሚስት
  • ፍየል መንታ ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
  • ፍየል መንታ ትወልድና አንዱ ለወናፍ አንዱ ለመጽሀፍ
  • ፍየል ሲሰባ ሾተል ይልሳል
  • ፍየል በልታ በበግ አበሰች
  • ፍየል በልታ በበግ አሳበበች
  • ፍየል ሲቀናጣ እናቱን ይሰራል
  • ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰራል
  • ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰር
  • ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
  • ፍየል ከቀዘነ ዲያቆን ከዘፈነ
  • ፍየል የለኝ ከነብር ምን አጣላኝ
  • ፍየልና ቀበሮ ምጥማጥና ዶሮ
  • ፍየሏን እንደበግ
  • ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
  • ፍዳ ለሀጥአን እሴት ለጻድቃን
  • ፍጥም አያናግር የጎርፍ ሙላት አያሻግር
  • ፍጥም አፍራሽ ቤተክርስቲያን ተኳሽ
  • ፍጥም ያቆማል እርቅ ይጠቀልላል
  • ፍጥም ያዋውላል አቧራ ያስላል
  • ፎክሮ መሸሽ ታሪክ ያበላሽ